ከ 7+ ዓመት በላይ የመካንነት ሕክምና ልምድ
16+ ዓመት የሕክምና ልምድ
የመካንነት ሕክምና፣ የ IUI ሕክምና፣ የ IVF ሕክምና፣ የ PCOS ሕክምና እና የማኅፀን እና ፅንስ ችግሮች ሕክምና
ለእያንዳንዱ ታካሚ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በሚስጥራዊ መንገድ አገልግሎት መስጠት
ለPCOS/PMOS የረጅም ጊዜ ክትትል እና አጠቃላይ እንክብካቤ
የ PCOS በአዲስ ቀላል አነስተኛ ወጪ በሚጠይቅ ውጤታማ የመካንነት ሕክምና
መደበኛ ያልሆነ የእንቁላል ማደግ እና መልቀቅ ችግር ላላቸው መፍትሔ መስጠት
ከታይሮይድ እና ፕሮላክቲን ሆርሞን ጋር የተያያዘ መካንነት ቀላል መፍትሔ መስጠት
የወንድ መካንነት ሙሉ ምርመራ እና የተሟላ ሕክምና
የሴት መካንነት ሙሉ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት
ዝቅተኛ እንቁላል ክምችት ላለባቸው ታካሚዎች ልዩ እንክብካቤ
ለእያንዳንዱ ታካሚ በግል የተበጀ የእንቁላል ማነቃቂያ አገልግሎት
የወንድ ዘር ፍሬ አዘጋጅቶ ወደ ማኅፀን ውስጥ በቀጭን ቱቦ የማስገባት ሕክምና
የወንድ እና የሴት የዘር ፍሬን ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች አዋህዶ ከ3-5 ቀናት ተንከባክቦ ወደ ማኅፀን ውስጥ የመመለስ ሕክምና
ተደጋጋሚ የዕርግዝና መቋረጥ ላለቸው መመርመር እና ማከም
የዘር ፍሬን ለወደፊት ለመጠቀም ወይም ከካንሰር ሕክምና ጋር ተያይዞ የሚመጣን መካንነት ለመከላከል ዘርን የማስቀመጥ ሕክምና
ለጥንዶች ከታቀደ ዕርግዝና በፊት የተሟላ የጤና ምርመራ እና ምክር መስጠት እንዲሁም ከወሊድ በኋላ የሚሰጡ የጤና እንክብካቤዎችን መስጠት
በመደበኛ የመካንነት ምርመራ ሁሉንም የመካንነት ምክንያቶች ማወቅ ይቻላል ማለት አይደለም። ሁሉም ምርመራዎች ጥሩ ናቸው ቢባልም፣ አንዳንድ የመካንነት ምክንያቶች በአሁኑ ጊዜ በሕክምናው ዓለም ላይ ባሉ መደበኛ ምርመራዎች ላይ ላይታዩ ይችላሉ:: ስለዚህ፣ እርግዝና ካልተከሰተ፣ ውድ የሆነውን የመውለድ ጊዜዎን ሳያባክኑ፣ ከቀላል ወደ ውስብስብ የሚሰጡ የመካንነት ህክምናዎችን ደረጃ በደረጃ በትክክለኛ ባለሙያ እየተከታተሉ መሄድ ይመከራል።
ብዙ ጥንዶች አይ ቪ ኤፍ (IVF) በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ቢደረግ ሁልጊዜም ሙሉ በሙሉ ስኬታማ የሚሆን ይመስላቸዋል። ነገር ግን የIVF ሕክምና ስኬት በአብዛኛው የተመሠረተው በሴቷ የእንቁላል ጥራት እና ብዛት ላይ ሲሆን፣ ይህም ከዕድሜ መጨመር ጋር አብሮ የመቀነስ ባሕሪ አለው። በመሆኑም በተፈጥሮ መንገድ ለማርገዝ ከአንድ ዓመት በላይ (ወይም ዕድሜዎ ከ35 በላይ ከሆነ ከስድስት ወር በላይ) ከሞከሩና ካልተሳካ፣ ጊዜ ሳይወስዱ ወደ ስፔሻሊስት ጋር መቅረብ ወሳኝ ነው። የIVF ሕክምናን ቀድሞ መጀመር ጥራቱና ብዛቱ የተሻለ የእንቁላል ክምችት ለማግኘት ስለሚረዳ የፅንስ መፈጠር እና የመውለድ ዕድልን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል።
ብዙ ጥንዶች እርግዝና በሚፈጠርባቸው ቀናት(ከ12-16 ባሉት ቀናት) ብቻ ግንኙነት ማድረግ እርግዝናን በፍጥነት ለማግኘት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ያምናሉ። ነገር ግን፣ የፒሲኦኤስ (PCOS) ችግር፣ የእንቁላል ክምችት ማነስ ወይም መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ዑደት ያላቸው ሴቶች ከእነዚህ ቀናት ቀድመው ወይም ዘግይተው እንቁላል ሊያመርቱ ይችላሉ። እንቁላል ከተመረተ በኋላ በሕይወት መቆየት የሚችለው ለ12–24 ሰዓታት ብቻ በመሆኑ፣ በዕለት ስሌት ላይ ብቻ መተማመን ለፅንስ ዝግጁ የሆነውን ትክክለኛውን ቀን እንዲያመልጥዎት ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ፣ የተሻለ ውጤት ለማግኘት የየራሳቸውን የእንቁላል ማምረቻ ዕለት ማወቅ አስፈላጊ ሲሆን፤ ለዚህም ወደ ወሊድ ስፔሻሊስት ዘንድ በመሄድ በማህፀን አልትራሳውንድ (Transvaginal Ultrasound) ክትትል ማድረግ አስተማማኙ መንገድ ነው።
በ ድረ-ገጹ አማካኝነት በ አካል እንዲሁም በስልክ ዶክተሩን ለማማከር ቀጠሮ ይያዙ።
ሁለቱም አማራጮች ይገኛሉ። ታካሚዎች በስልክ (ለ20 ደቂቃ) ወይም በአካል በክሊኒኩ መጥተው ማማከር ይችላሉ።
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች:
ማዕዶት መካከለኛ ክሊኒክ ፤ አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ
ቅጹን ይሙሉ፤ አስተያየቶችን በቅርቡ ያገኛሉ።